በኩታበር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ቡድን ለአጠቃላይ የጽ/ቤቱ  ሰራተኞች እና ለቀበሌ ስራ አስኪያጆች  የግንዛቤ  ፈጠራ አካሂዷል፡፡

ከቀበሌ ስራ አስኪያጆች እና ለጽ/ቤት ሰራተኞች  ስለ ድጅታል ኢትዮጵያ ና ስለ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ስለተለሙ ሲስተሞችና ስለ አጠቃቀማቸው ስልጠና አዘል የግንዛቤ ፈጠቃ  መስጠት ተችሏል፡፡

የኩታበር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወር ከአጠቃላይ የጽ/ቤቱ  ሰራተኞች እና አጋር አካላት ጋር የ ስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡

ከቀበሌ ስራ አስኪያጆች እና ከ ጽ/ቤት ሰራተኞች ጋር አጠቃላይ በስድስት ወሩ በሁሉም ቡድኖች የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ጥሩ አፈጻጸም ያመጡ ሰራተኞችን የእውቅና ሰርትፊኬት መስጠት ተችሏል፡፡

የኩታበር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የእቅድ ትውውቅ

የኩታበር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የእቅድ ትውውቅ ተካሂዷል፡፡ የ2017ዓ.ም የስራ አፈጻጸምን ከጽህፈት ቤቱ ባለሙያወች፣ከስራ አስኪያጆች እና አጋር አካላት ጋር በመገምገም የተሰሩትን ስራወች በማበረታታት እና ያልተሰሩትን ስራወች በቀጣይ የ2018 ዓ.ም እቅድ ጋር በማካተት በማቀድ ለቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት በእቅድ ትውውቁ ለይ ተገልጿል፡፡